Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ከግሎባል ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ጋር የጤና ተቋማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከግሎባል ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጋቪ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ጋር በመሆን የጤና ተቋማትን ጎብኝተዋል።

ሚንስትር ዴኤቷ ከግሎባል ፈንድ ዋና ዳይሬክተርና ከጋቪ የቦርድ ሰብሳቢ ጋር በመሆን የጤና ተቋማት በኤችአይቪ ኤድስ፣ ቲቢ፣ ወባ እና ክትባት ዙርያ እየሰጡ የሚገኙትን አገልግሎት ነው የጎበኙት።

የጤና ሚኒስትሩ ዶክትር አሚር አማን ግሎባል ፈንድስ እና ጋቪ ከኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ጋር ላላቸው ውጤታማ አጋርነት አመስግነዋል።

በተጨማሪም ከሁለቱ ተቋማት ጋር በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

You might also like
Comments
Loading...