Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 19 ሚሊየን ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛት 19 ሚሊየን መድረሱን ኢትዮቴሌኮም አስታወቀ።

ኢትዮቴሌኮም ይህንን ያስታወቀው ያለፉትን ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

በዚህም የቴሌኮሙ ተጠቃሚ ብዛት 41 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱንም ገልጿል።

በሞባይል ድምጽ 39 ነጥብ  54 ሚሊየን፣ መደበኛ ስልክ 1 ነጥብ 14 ሚሊየን፣ በስድስት ወራቱ ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚ 426 ሺህ ሲሆን፥ አጠቃላይ የዳታና የኢንተርኔት ተጠቃሚ ደግሞ 19 ነጥብ 49 ሚሊየን መድረሱን ይፋ አድርጓል።

በተጨማሪም አጠቃላይ የቴሌኮም ተደራሽነት 43 በመቶ መድረሱንም በስራ አፈጻጸሙ መግለጫ ላይ አንስቷል።

ቴሌኮሙ በመፈንቅ ዓመቱ ካስገባው 16 ነጥብ 71 ቢሊየን ብር ውስጥ ሞባይል 63 ነጥብ 2 በመቶውን ሲሸፍን፥ ዳታና ኢንተርኔት 28 ነጠብ 7 በመቶውን እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ድርሻ 5 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ ማስመዝገቡን ጠቅሷል።

ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት የኢንተርኔት አገልግሎት የማገኘት መጠንም 97 ነጥብ 12 በመቶ እንደነበረም በመግለጫው አንስቷል።

 

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...