Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልለ የታክስ ንቅናቄ መድረክ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣የካቲት 5፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የታክስ ንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

የታክስ ንቅናቄ መድረኩን የገቢዎች ሚንስቴር ሚንስትር ወይዘሮ  አዳነች አቤቤ  እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ አስጀምረውታል ።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅትም ስለ ታክስ ንቅናቄው ምንነትና ፋይዳ  ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ የተለያዩ ተቋማትንና የህብረተሰብ ክፍሎችን ወክለው የተገኙ አካላትም በቀጣይ በታክስ ጉዳይ ላይ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ሊያደርጉት ይገባል ያሉዋቸውን የተለያዩ ሀሳቦች አስተላልፈዋል።

በታክስ አምባሳደርነት የተመረጡ ግለሰቦችም በታክስ ስርዓቱ ውጤታማነት ላይ በቀጣይ የሚኖራቸውን አስተዋጽፅኦ በመግለጽ ቃል ኪዳን መግባታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘናው መረጃ ያመላክታል

You might also like
Comments
Loading...