Fana: At a Speed of Life!

የኪምና የዱቴርቴ አምሳያዎች የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎችን ሲያስገርሙ ውለዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰሜን ኮርያው ፕሬዚዳንት እና የፊሊፒንሱ አቻቸው ሮድሪጎ ዱቴርቴ አምሳያዎች በሆንግ ኮንጎ ጎዳዎች ላይ ሲንሸራሸሩ ውለዋል።

በነገሩ እጅግ የተገረሙ የከተማዋ ነዋሪዎችም ከኪምና ከዱቴርቴ አምሳያዎች ጋር ፎቶግራፍ ለመነሳት መጠነኛ ግርግር መፍጠራቸው ተነግሯል።

እንዲሁም የሁለቱ አምሳያዎች የተለያዩ ፎቶግራፎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ለመሆን በቅተዋል።

የፕሬዚዳንቶቹ አምሳያዎች መጀመሪያ የታዩት ሆንግ ኮንግ በሚገኝ የፊሊፒንሶች ምግብ ቤት መሆኑም ተነግሯል።

የታዩበት አካባቢም የደቡብ ምስራቅ እስያ ሰራተኞች የሚበዙበት ሲሆን፥ ዕለቱም የእረፍት ቀናቸው እንደነበረ ተገልጿል።

በርግጥ ባለፈው ዓመት ይፋዊ ባልሆነ ጉብኝት በምግብ ቤቱ ውስጥ እውነተኛው የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ መታየታቸው ይነገራል።

የኪም አምሳያ የ22 ዓመት ወጣት ሲሆን ሆንግ ኮንግ የተወለደ አውስትራሊያዊ መሆኑ ተገልጿል።

የዱቴርቴ አምሳያ በበኩሉ ከሆንግ ኮንግ ሲወጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን የአምስት ልጆች አባት መሆኑ ተጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የኪም አምሳያዎች በሲንጋፖር ጎዳናዎች ላይ መታየታቸው የሚታወስ ነው።

 

ምንጭ፦ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...