Fana: At a Speed of Life!

ዋትስአፕ በፊት ገጽታና ጣት አሻራ መቆለፍ የሚያስችል አገልግሎት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዋትስአፕ  መተግበሪያ በፊት ገጽታና ጣት አሻራ መቆለፍ የሚያስችል አገልግሎት ይፋ አደረገ፡፡

መተግበሪያው ደንበኞቹ ከተጠቀሙበት በኋላ በራሱ ሚቆልፍ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ባለቤትነቱ የፌስቡክ ኩባንያ የሆነው ዋትስአፕ አዲሱ መተግበሪያው ደንበኞቹ የተለዋወጡትን መዕልክት ወዲያዩኑ በመቆለፍ በቀላሉ ከተጠቃሚዎቹ ውጭ መረጃው ለ3ኛ ወገን እንዳይተላለፍ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ይህን አገልግሎትም አይፎን ኤክስ ወይም በጣት አሻራ በሚሰሩና እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ ገበያ ላይ በዋሉ ስማርት ስልኮች ማግኘት እንደሚቻል ነው በዘገባው የተገለጸው፡፡

በኢሜል “ኖትፊኬሽን” የሚሰራ የአንድሮይድ መተግበሪያ ተመሰሳይነት ያለው አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- cnet.com

You might also like
Comments
Loading...