Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ ኡማና አርቲስቶች ከጎዳና ወደ ማገገሚያ ማዕከል የገቡ ልጆችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማና አርቲስቶች ከጎዳና ወደ ማገገሚያ ማዕከል የገቡ ልጆችን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የማህበራዊ ትረስት ፈንድ የቦርድ አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ኑሮዋቸውን የመሰረቱ ዜጎችን ወደ ማዕከላት የማስገባት ስራ ጥር 26 ቀን 2011 አመተ ምህረት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱ ወደ ማዕከላቱ የማስገባት ስራውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከኡ ኡማ ፣ የማህበራዊ ትረስት ፈንድ የቦርድ አባላት እና የከተማው በጎ ፈቃድኛ ወጣቶች አስጀምረው ነበር፡፡

ወደ ማዕከል ለመግባት ፈቃደኛ ለሆኑ ብቻ ቅድሚያ በመስጠት እንደተጀመረም ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like
Comments
Loading...