Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካአውያን ለስደተኞች ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አፍሪካአውያን ለስደተኞች ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቶሬዝ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመምበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ጋር በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዛሬ በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ አፍሪካአውያን የስደት መንስኤዎችን በማጥናት ለስደተኞች ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጡ እንደደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በአህጉሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ዘላቂ በማድረግ በምርጫና ሌሎች ምክንያቶች የሚፈጠሩ ግጭቶችን በውይይት በመፍታት ዜጎቻውን ከስደትና መፈናቀል ሊታደጉ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ዋና ጸሃፊው የስደትን ጉዳይ በተመለከተ ሲያብራሩ አሁን ላይ ከአፍሪካ ወደ ተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚሰደዱ ዜጎች ቁጥር ይልቅ ከአንድ አፍሪካ ሀገር ወደሌላኛው የአፍሪካ ሀገር የሚሰደዱትእንደሚበለልጡ ነው የተናገሩት፡፡

ከፍተኛ ጉዳት እያጋጠማቸው ያሉት ግን ከአፍሪካ ወደ አውሮፓና ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ባህር አቋርጠው በህገ ወጥ መንገድ የሚጓዙት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በአፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች የሰላምና ደህንነት ተስፋዎች እየታዩ መሆኑን የተናገሩት ዋና ጸሃፊው የኢትዮ- የኤርትራ፣ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎችን የሰላም ስምምነቶችን አንስተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመሆን በአህጉሪቷ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍ ስትራቴግጅ አጋርነት መስርቶ እተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ለለውጡ ያን ያህል ድርሻ የሌላትአፍሪካ ላይ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመምበር ሙሳ ፋኪ መሃመት በበኩላቸው አፍሪካዊያን ለስደተኞች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ህብረቱ አቅጣጫ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ነገ የሚጀመረው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ዋና ትኩረቱን ዘላቂ መፍትሄ ለስደተኞች፣ ስደት ተመለሾችና ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

በስላባት ማናዬ

You might also like
Comments
Loading...