Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት የናይጄሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደሚመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት የናይጄሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደሚመሩ ተገለጸ ፡፡

የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት የናይጄሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደሚመሩ ተገልጿል፡፡

ለዚህም አፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሀመት የአፍሪካ ህብረት የናይጄሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን ወደ ናይጄሪያ ለመላክ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች  ኮሚሽነር ሚናታ ሳማታ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2018 በተመሳሳይ መልኩ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ  ቡድን በዝምባብዌ መምራታቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like
Comments
Loading...