Fana: At a Speed of Life!

በ2018 በአውሮፓ ሀገራት የኩፍኝ በሽታ የስርጭት መጠን ከፍተኛ እንደነበር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የነበረው የኩፍኝ በሽታ የስርጭት መጠን ከፍተኛ እንደነበር የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

በሽታው በሀገራቱ የነበረው የስርጭት መጠን ከ2017 ጋር ሲነጻጸር በሶስት እጥፍ ማሻቀቡን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል።

በዚህም መሰረት በ2018 በሀገራቱ በበሽታው ተይዘው የነበሩ ሰዎች ቁጥር ከ82 ሺህ በላይ መድረሱ ነው የተገለፀው።

የኩፍኝ በሽታ በቫይረስ አማካይነት የሚተላለፍ ሲሆን፥ የሳንባና የአዕምሮ በሽታን ጨምሮ የተለያዩ የጤና እክሎችን ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው።

በሽታው በፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዩክሬንና ግሪክን ጨምሮ በሌሎች 10 የአውሮፓ ሀገራት ላይ በብዛት ተሰራጭቶ እንደነበርም ድርጅቱ ገልጿል።

ከእነዚህ ሀገራት መካከል በዩክሬን የነበረው የስርጭት መጠን ከፍተኛው ሲሆን፥ በሽታው ከ1 ሚሊየን ሰዎች ውስጥ በ1 ሺህ 500 ያህሉ ይገኛልም ነው የሚለው መረጃው።

በሀገሪቱ የነበረው የስርጭት መጠን ከ2017 ጋር ሲነፃፀርም በ10 በመቶ ጭማሪ አሳይቷልም ነው ያለው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...