Fana: At a Speed of Life!

በፕሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል አቻ ሲለያዩ ድሬዳዋ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስራ አራተኛ ሳምንት በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል፡፡

ድሬደዋ ከተማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

ድሬደዋ ከተማ ከሜዳው ውጭ ሶስት ወሳኝ ነጥብ እንዲያገኝ ያስችለውን ግብ ገናናው ረጋሳ ጨዋታው በተጀመረ በሶስተኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ቅድስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው አብድሩሃማን ሙባረክ በ24 ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ ፋሲል ከነማ ቀዳሚ ሲሆን ሙሉአለም መስፍን የቅዱስ ጊዮርጊስን የአቻነት ግብ በ40ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዡን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ25 ነጥብ ሲመራ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና በእኩል 23 ነጥብ  በጎል  ብልጫ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

You might also like
Comments
Loading...