Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተገነባው የፍትህ አካላት የባለሙያዎች ስልጠና ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተገነባው የፍትህ አካላት የባለሙያዎች ስልጠና ማዕከል ተመረቀ።

በአውሮፓ ህብረት በ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ የተገነባው የፍትህ አካላት የባለሙያዎች ስልጠና ማዕከል በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

ማዕከሉ በሃያት አካባቢ በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፥የአካዳሚክ ስልጠና ማዕከል፣ የሰልጣኞች ማደሪያን እና የአስተዳደር ቢሮን ያካተ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ማዕከሉ ለዳኞችና ዓቃቤ ህጎች ስልጠና  የሚሠጥበት መሆኑ ነው የተገለፀው።

በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ተወካይ አምባሳደር ዮሃን ቦርግሰተን የአውሮፓ ህብረት በቀጣይም የሁለተኛው ምዕራፍ የማስፋፊያ ግንባታ እና የፍትህ  ስርዓት ማሻሻያን ለማገዝ ቃል ገብተዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝን ጨምሮ የክልል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተግኝተዋል።

የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕከልፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አበባው ጌታነህ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ማዕከሉ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን ተናግረዋል።

በታሪከ አዱኛ

You might also like
Comments
Loading...