Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ለፕሬዚዳንት ትራምፕና ኪም ዳግም ግንኙነት ዝግጅት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ለፕሬዚዳንት ትራምፕና ኪም ዳግም ግንኙነት ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

በሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛው ስቴፈን ቤገን የአማሪካና በሰሜን ኮሪያ መሪዎች ዳግም ስብሰባ ዙሪያ ለሶስት ቀናት ሲመክሩ ቆይተው መመለሳቸው ተነግሯል፡፡

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ስቴፈን ቤገን የሰሜን ኮሪያው አቻቸውን ኪም ህዮክ ቾልን ዳግም እንደሚያገኙዋቸውም ነው የተነገረው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናል ትራም ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆን ኡን ጋር እንደ አውሮፓአዊያኑ አቆጣጠር ከየካቲት 27 እስከ 28 ቀን 2019 ዓ.ም በቬትናም ሃኖይ ፊት ለፊት እንደሚገናኙም አረጋግጠዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ተወካያቸው ስቴፈን ቤገን ከሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡን ጋር ዳግም የሚካሂዱትን ስብሰባ ቦታና ቀን በፒያንያንግ በመወሰን ውጤታማ ውይይቶችን አድረገው ከ3ቀናት በኋላ ተመልሰዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ

You might also like
Comments
Loading...