Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለመብራትና ውሃ አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል ደንበኞች እየተጉላሉ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣የካቲት 5፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የመብራትና ውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመፈፀም ደንበኞች እየተጉላሉ መሆኑ ተገለፀ።

ለተገልጋዮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የመብራትና የውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመፈፀም ጣቢያዎች በሚያቀርቧቸው የተለያዩ ችግሮች ሳቢያ  እየተጉላሉ መሆኑን ተናግረዋል ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከትናንት ጀምሮ በተለያዩ የክፍያ ጣቢያዎች ተግኝቶ ባደረገው ምልከታ ፥ከሶስት በላይ የክፍያ ጣቢያዎች በኔትወርክና ጄኔሬቴር መቋረጥ ምክንያት  አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአንዳንድ ጣቢያዎች በተከሰተው ጊዜያዊ ችግር  ምክንያት  ደንበኞች ምንም አገልግሎት ሳያገኙ እንዲመለሱ መደረጉን ነው መመልከት የተቻለው።

ከዚህ ባለፈም በመዲናዋ በሚገኙ የተወሰኑ የለሁሉ የክፍያ  ጣቢያዎች ላይ ደንበኞች ረጃጅም ሰልፎችን  ተሰልፈው ለማየት ተችሏል ።

 

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ የኤሌትሪክ አገልግሎት ከፋዮች መጉላላትን ለመቅረፍ እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይ ወር ተግባራዊ የሚሆን በክፍያ ጣቢያዎች በባንክና ስልክ ለመክፈል የሚያሰችል አሰራር ይዘረጋል ብለዋል።

የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ  አርጋው በበኩላቸው የውሃ ደንበኞች በክፍያ አገልግሎት ችግርን ለመፍታት እየሰራን ነው ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ኤክሲኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጨረር አክሊሉ በየለሁሉ የሚከናወን የክፍያ ችግር በዘለቄታም ሆነ በአጭር ጊዜ እንዲፈቱ የኔትወርክ ስርዓቱን በመፈተሽ  ችግሩን ለመቅረፍ እሰተሰራ ነው ብለዋል።

 

በታሪክ አዱኛ

You might also like
Comments
Loading...