Fana: At a Speed of Life!

በሌላው አለም የማይገኙና በኩባ ብቻ የሚመረቱ የሰውና የእንስሳት መድሃኒቶችን ኩባ  ኢትዮጵያ ውስጥ ልታመርት ነው

አዲስ አበባ፣ጥር 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሌላው አለም የማይገኙና በኩባ ብቻ የሚመረቱ የሰውና የእንስሳት መድሃኒቶችን ኩባ  ኢትዮጵያ ውስጥ ልታመርት ነው፡፡

በሌላው አለም የማይገኙና በኩባ ብቻ የሚመረቱ የሰውና የእንስሳት መድሃኒቶችን ኢትዮጵያ ውስጥ በማምረት ለኢትዮጵያና አፍሪካ ገበያ ለማቅረብ ከዚህ በፊት ስምምነት ላይ መድረሷን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ለዚህም በኩባ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ድራ ሲዲ ሳሉደ ማርዚያ የተመራ ልዑክ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡

የካንሰር በሽታን ባለበት የሚያቆይ መድሃኒትና እንስሳት ጥገኛ ህዋሳትን ለመከላከል የሚያስችሉ መድሃኒቶችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ኩባ ዝግጅት ላይ መሆኗን ልዑካኑ ተናግረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ እንደገለጹት÷ የመድሃኒት ፋብሪካው በኢትዮጵያ ውስጥ መከፈት የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ፣ የሰው ሃብት ልማት ለመፍጠርና ኢትዮጵያን የልዩ መድሃኒት ማምረቻ ሀገር ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

You might also like
Comments
Loading...