Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ለደስታ የተተኮሰው ጥይት የሙሽሪትን ህይወት ቀጠፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጎንደር ለደስታ የተተኮሰው ጥይት የሙሽሪትን ህይወት ቀጠፈ።

አሳዛኙ ድርጊት የተከሰተው በትናትናው ዕለት በጎንደር ከተማ አስተዳር አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ነው ተብሏል።

ሰርጉን ድምቅት ለማላበስ የተተኮሰው ጥይትም ደስታውን ወደ ሐዘን መቀየሩ ተነግሯል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ተወካይ ምክትል ኃላፊ አቶ ገብረኢየሱስ ወንድሙ ጉዳዩን ለመመርመር ከጎንደር ከተማ አስተዳደርና ከአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ቦታው መላካቸውን ጠቅሰዋል።

ምክትል ኃላፊው አሳዛኙ ክስተት የመሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ችግርና ክልከላን የመተላለፍ ውጤት መሆኑንም ተናግረዋል።

በጎንደርና አካባቢው ባለፈው ሳምንት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ ከፀጥታ አካላት ውጪ የጦር መሳሪያ መያዝና መንቀሳቀስ መከልከሉ ይታወሳል።

ምንጭ፦አብመድ

You might also like
Comments
Loading...