Fana: At a Speed of Life!

በብሪታኒያ መንግስት የተነሳበትን የደህንነት ስጋት ለመቅረፍ 2 ቢሊየን ዶላር የመደበው ሁዋዌ ከ3-5 አመት ያስፈልገኛል አለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁዋዌ በብሪታኒያ መንግስት የተነሳበትን የደህንነት ስጋት ለመቅረፍ 2 ቢሊየን ዶላር ማዘጋጀቱን የገለፀ ሲሆን፥ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት እንደሚያስፈልገው ይፋ አድረጓል፡፡

በዓለም ትልቁ የቴሌኮም መሳሪያዎች አምራች የሆነው ሁዋዌ ከቻይና መንግስት ጋር ባለው ግንኙነት ምክንያት ከምዕራባውያን ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ይገኛል፡፡

በተለይ አሜሪካና አጋሮቿ ኩባንያው የሚያመርታቸው መሳሪያዎች በቻይና መንግስት ለስለላ ይውላሉ የሚል ወቀሳ ያቀርባሉ፡፡

ሆኖም በጉዳዩ ዙሪያ ይፋዊ መረጃ እንዳልተገኘ የተገለፀ ሲሆን፥ ኩባንያውም የሚቀርብበታ ቅሬታ በተደጋጋሚ ያስተባብላል፡፡

ኩባንያው ለብሪታኒያ የህግ ባለሙያዎች በላከው ደብዳቤ በቴክኒካል እና አቅርቦት ትስስር ዘርፉ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ 2 ቢሊየን ዶላር የመደበ ቢሆንም ውጤታማ ስራ ለማከናወን ከሶስት እስከ አምስት እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡

የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ አቅሙን የማሻሻል ስራው ውስብስብ እና ብዙ ሂደቶች ያሉት በመሆኑ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ቢያንስ ሶስት አመታት ያስፈልገኛል ብሏል ኩባንያው፡፡

ምንጭ፡-abs-cbn

You might also like
Comments
Loading...