Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውና ጥቅም ላይ የማይውሉ የህክምና ግብዓት ማስወገጃ ኢንሲኒሬተር ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈና ጥቅም ላይ የማይውሉ የህክምና ግብዓት ማስወገጃ ኢንሲኒሬተር በአዳማ ተመረቀ፡፡

ማዕከሉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን መርቀው ከፍተውታል፡፡

በሀገሪቱ መጀመሪያ የሆነውን ኢንሲኒሬተር የመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ነው ያስመረቀው፡፡

ኤጀንሲው የደህንነት መቆጣጠሪያ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ እና የመግቢያ በር መቆጣጠሪያ መሳሪያ መያዙ ተገልጿል፡፡

የተቋሙ 189 ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴያቸውን መለየት የሚያስችል መሳሪያ (GPS) እንደተገጠመላቸው ተነግሯል፡፡

ይህም ወደ ጤና ተቋማት የሚሄደውን የመድሐኒት ስርጭት የተሻለ እንደሚያደርገው ዶክተር አሚር አማን ገልጸዋል፡፡

You might also like
Comments
Loading...