Fana: At a Speed of Life!

በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ጥር 2፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ፌሊክ ቲሽሴክዲ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡

ቲሽሴክዲ ከ18 ሚሊየን የምርጫ ካርዶች 38 ነጥብ 5 በመቶውን በማግኘት ነው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ያሸነፉት፡፡

ተመራጩ ፊሊክስ   ቲሽሴክዲ    ከ7 ሚሊየን ድምጽ  በላይ በማግኘት ያሸነፉ ሲሆን ዋነኛው ተፎካካሪ ፋዩሉ 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ድምፅ አግኝተዋል፡፡

ዋነኛው ተፎካካሪና በተቃዋሚዎች የሚደገፈው ማርቲን ፋዩሉ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል፡፡

ፋዩሉ በቅድመ ምርጫ ወቅት በተደረገ ቆጠራ  ቀዳሚ እንደነበሩ ነው መረጃዎች ያመለከቱት፡፡

ለረጅም ጊዜ ሀገሪቱን በማስተዳደር በቆዩት ጆሴፍ ካቢላ የሚደገፉት ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪይ  4 ነጥብ 4 ሚሊየን ድምፆችን በማግኘት በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ግጭት ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት የሀገሪቱ ፓሊስ በኮሚሽኑ መስሪያ ቤት  የታጠቁ ፓሊሶች አሰማርቷል፡፡

አዲሱ ፕሬዚዳንት ከፈረንጆቹ 2001 ጀምሮ ሀገሪቱን ሲመሩ ከነበሩት ጆሴፍ ካቢላ ስልጣኑን በቅርቡ ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሀገሪቱን  ወደ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ለማሸጋገር ከፍተኛ እምነት የተጣለበት ይህ ምርጫ ከአውሮፓውያኑ 2016 ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲራዘም መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...