Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል ስላለው ታሪካዊ ግንኙነት ዙሪያ ላይ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም በቀጣይ በሃገራቱ የትብብር ቁልፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ ላይም ውይይት አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ማታሬላ በአሁኑ ወቅት ያለውን ለውጥና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እየተጫወተች ያለውን ሚና አድንቀዋል።

በተያያዘ ዜና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ አቻቸው ጊሴፔ ኮንቴ ጋር እየተወያዩ ነው።

መሪዎቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመምከር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ወደ ጣሊያን ማቅናታቸው ይታወሳል።

በቆይታቸውም ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

 

 

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው፤

You might also like
Comments
Loading...