Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስዊዘርላንድ ዳቮስ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስዊዘርላንድ ዳቮስ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በሚካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው ወደ ስፍራው ያቀኑት።

በፎረሙ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ሃገራት መሪዎች በተገኙበት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በንግግራቸውም በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ስለተደረጉ ማሻሻያዎችና ለውጦች ያነሳሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

የተለያዩ ሃገራት እና ቢዝነስ መሪዎች በስዊዘርላንዷ ዳቮስ ከተማ በየአመቱ በመገናኘት በወደፊቱ የዓለም ኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ይመክራሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከትናንት በስቲያ ወደ ጣሊያን በማምራት በሮም የሁለት ቀናት ቆይታ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በጣሊያን በነበራቸው ቆይታም ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም ካጣሊያኑ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር እንዲሁም ከሮማው ሊቀጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ ጋር በመወያየት የጣሊያን ቆይታቸውን አጠናቀው ዛሬ ዳቮስ ገብተዋል።

 

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው

You might also like
Comments
Loading...