Fana: At a Speed of Life!

የካንሰር በሽታን በትንፋሽ ማወቅ የሚያስችል ሙከራ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተለያዩ የካንሰር በሽታ አይነቶችን በትንፋሽ ማወቅ የሚያስችል ሙከራ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ፡፡

የተለያዩ የበሽታ ምልክቶችን በሰውነት ጠረን ማወቅ እንደሚቻል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በሃገረ እንግሊዝ የሚገኙ ተመራማሪዎችም ካንሰርን በትንፋሽ መለየት የሚያስችል ሙከራ ሊያደርጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሙከራ ደረጃ ይጀመራል የተባለው ይህ የካንሰር መለያ ዘዴ ከተለያዩ ሰዎች ናሙናዎችን በመውሰድ የሚደረግ ይሆናልም ነው የተባለው።

የትንፋሽ መለያ ሙከራው ከደምና ከሽንት ምርመራ ጋር አብሮ ጎን ለጎን የሚሄድ ይሆናልም ነው የተባለው።

ይህም የካንሰር በሽታው ያለበትን ደረጃ ለመለየትና ምናልባትም ስር ሳይሰድ ለመለየት እንዲያግዝ መሆኑም ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው ወጤታማ የሚሆን ከሆነ ሰዎች ተጨማሪ ህክምና እንዲያገኙ ለመጠቆምና ለመወሰን ይረዳልም ነው የተባለው።

ለዚህ የምርመራ ሂደትም ከ1 ሺህ 500 ሰዎች የትንፋሽ ናሙናዎች የሚወሰዱ ይሆናል።

የዚህ ምርመራ ውጤት ግን በርካታ ጊዜን እንደሚወስድም ተገልጿል።

የበሽታ ምልክቶችን በትንፋሽ መለየት የሚቻል ሲሆን፥ በታይፎድ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ከሰውነታቸው የተጋገረ ዳቦ አይነት ጠረን እንዲሁም በስኳር በሽታ የተጠቁ ሰዎች ደግሞ የበሰበሰ አፕል አይነት ትንፋሽ እንዳላችው ተመልክቷል፡፡

 

 

 

ምንጭ፡-ቢቢሲና ሲ ኤን ኤን

You might also like
Comments
Loading...