Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ደንብ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ደንብ አፀደቀ፡፡

እንደገና የተቋቋመው የይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን ተገልጋዮች ከግብር አገልግሎት ጋር በተያያዘ ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ ግብር ከፋዩን የሚያጉላሉ አሰራሮችን በማስቀረት ከወቅቱ ጋር የሚሄድ የአደረጃጀት ለውጥ መድረጉ ተገልጿል፡፡

ለዚህም ለንግዱ ማህበረሰብ ቅሬታ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚስችል የይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን እንደገና ለማቋቋም የሚያስችል ደንብን መጽደቁ ነው የተገለጸው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን ዝርዝር መመርያ የአቃቤ ህግ ቢሮ እንዲያዘጋጅ ና የታክስ አሰባሰብ ና ትመና ላይ ያለውን ቅሬታ ለመቅረፍ ኮሚሽኑ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ ወስኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽኅፈት ቤት መረጃ እንደሚያመላክተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከመርካቶ ና አከባቢው ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር በተወያዩበት መድረክ ላይ ከተነሱ ቅሬታዎች መካከል አንደኛው የታክስ ትመና ስርዓቱ ላይ ያለው ቅሬታ እንደነበር ይታወሳል፡፡

You might also like
Comments
Loading...