Fana: At a Speed of Life!

የበረዶ ግግር በአውሮፓ እንቅስቃሴ አስተጓጉሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ የበረዶ ግግር እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ተገለጸ፡፡

ሰሞኑን በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች እየጣለ ያለው የበረዶ ግግር በከፊል ጀርመንና ስዊድን የሰዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መግታቱ ተነግሯል፡፡

በበረዶ ግግሩ መንገዶች መዘጋታቸው፣ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡንና ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በደቡብ ጀርመን የባቫሪያን ግዛት እንዲሁም በሰሜናዊ ስዊድን የበረዶ ግግሩ ለመንገዶች መዘጋት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።

በባቫሪያ የባቡር ትራንስፖርት የተቋረጠ ሲሆን÷ በትናንትናው ዕለት በበረዶ ምክንያት የወደቀ ዛፍ አንድ የዘጠኝ አመት ልጅ መግደሉ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ ሰሜናዊ ስዊድን በከባድ የበረዶ ውሽፍንር ምክንያት መንገዶች መዘጋታቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በተመሳሳይ መልኩ በአውስትራሊያ በጣለው በረዶ በሳፍነው ሳምንት ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ሁለት ተጓዦች አድራሻቸው ጠፍቷል ተብሏል።

ምንጭ ፡- ቢ ቢ ሲ

You might also like
Comments
Loading...