Fana: At a Speed of Life!

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ጥር 2፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች  እና ሕገ መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከልን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ቀረበ።

ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በዚህም ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተላኩ ረቂቅ አዋጆችን እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተደረሱ ስምምነቶች ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እና  ሕገ መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከልን ለማቋቋም የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን  መርምሮ ለሚመለከታቸው  ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ለቋሚ ኮሚቴ የተመራው የሕገ መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ረቂቅ አዋጅ   ዜጎች በህገ መንግስታዊና በፌዴራሊዝም ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት፣  የመቻቻል ባህልን ለማጎልበት እና  ሀገራዊ እሴቶችን ለማዳበር ያላው ሚና የላቀ  ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ የዜጎችን ለህጋዊ አላማ የመደራጀት መብት ለማረጋገጥ ፣ በሀገሪቱ ልማትና ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያላቸው ሚና እንዲጎለብት ለማድረግ ፣የተመቻቸ ምህዳር ለመፍጠር፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ተጠያቂነትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳል ተብሏል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ባዛሬው ውሎው ከሞሮኮ መንግስት ጋር በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፣ ጥበቃ ዘርፍ፣ ግብርና ዘርፍ  እንዲሁም  ከሩዋንዳ ጋር በኮሙኒኬሽን ኢንፎርሜሽንና ሚዲያ እና በግብርና ዘርፍ   ተደረሱ የትብብር ስምምነትቶችን አፅድቋል።

እንዲሁም  ከተለያዩ ሀገራት የተፈረሙ ስምምነቶች ለማጽደቅ የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን  ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

አወል አበራ

You might also like
Comments
Loading...