Fana: At a Speed of Life!

ወላጅ እናቷን ለማስደስት እራሷን ያጠፋችው ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ጥር 02፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በሜክሲኮ ወላጅ እናቷን በዓለም ደስተኛዋ ሴት እንድትሆን በማሰብ  እራሷን  ያጠፋችው ታዳጊ  ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።

በዓለም ላይ ሰዎች የሚወዱትን ሰው ለማስደሰት የተለያዩ ነገሮችን በስጦታ መልክ አሊያም በፅሁፍ ወይም በቃል አማካይነት ስሜታቸውን ይገልፃሉ።

አለፍ ሲልም ሰዎች የሚወዱት ሰው አንዳች ችግር እናዳይደርስበት  ሲሉ እራሳቸውን አሳልፈው ሊሠጡም ይችላሉ።

ሜክሲኳዊታ የ10 ዓመት  ታዳጊ ኢቨለይን ኒኮሌ ያደረገችውም ከዚህ የተለየ አይደለም ።

ታዳጊዋ እናቷን በዓለም ደስተኛዋ ሴት እንድትሆን በመመኘት እራሷን ማጥፋቷ ተነግሯል።

ታዳጊዋ ከመሞቷ በፊት በፃፈችው መልዕክትም  ወላጅ አባቷ  ቤተሰቡን ጥሎ የጠፋው በእሷ  ምክንያት መሆኑን እንደምታምን ገልፃለች ።

ስለሆነም የቤተሰቧንና የእናቷን ዘላለማዊ  ደስታ ለመመለስ እራሷን መስዋዕት ለማድረግ መወሰኗን አስፍራለች ።

በተለይም ከተወለደች ጀምሮ  ወላጅ እናቷ  ደስተኛና ጥሩ ህይወት  እንዳትኖር ምክንያት መሆኗን በመጥቀስ ፥ፈጣሪ  ለእናቷ  ቀሪ ዘመኗን የተደላደለና ደስተኛ እንዲያደርግላት ተመኝታለች።

 

 

ምንጭ፦ዘ ሰ ን

You might also like
Comments
Loading...