Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ስምምነት ላይ ደርሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የኢትጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥን ያካተተና በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ የልኡካን ከሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ሚኒስትር ሞሃመድ አል ጀደንና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ባደረገው ወይይት ሁለቱ ሀገሮች የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ትብብራቸውን ለማጠናከር ስምምነት ለይ መድራሰቸው ተገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክትው የልኡካን ቡደኑ ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ባደረገው ውይይት ሁለቱ ሀገራት በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በኃይል ልማት፣ በማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍና በንግድ ያላቸውን የቆየና የካበተ የኢኮኖሚ ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡

የሳዑዲ አረቢያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ኢንቨስትመንት አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ድጋፉን አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

አቶ አህመድ ሽዴ በሳዑዲ በነበራቸው ቆይታ ከሳዑዲ አረቢያ አካባቢ ጥበቃና ውሃ ሚኒስትር አብዱልረህማን ቢን አል ፋድሊ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከሳዑዲ ልማት ፈንድ አመራሮችና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዝርዝር በኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው።

ሳዑዲ አረቢያ ሶስተኛዋ የኢትዮጵያ የንግድ ሸሪክ ስትሆን፣ ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱት በ1941 ዓ.ም መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

You might also like
Comments
Loading...