Fana: At a Speed of Life!

ትንፋሻችንን በመለካት ምን መመገብ እንዳለበን የሚነግረን መሳሪያ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትንፋሻችንን በመለካት ምን አይነት ምግብ መመገብ እንዳለብን የሚጠቁሙን ሁለት መሳሪያዎች ለእይታ ቀርበዋል።

አነስተኛ መጠን ያላቸው እነዚህ የቴክኖለጂ ፈጠራዎች በአሜሪካዋ ላስ ቬጋስ በተካሄደ አውደ ርእይ ላይ ለእይታ መቅረባቸውም ተነግሯል።

መሳሪያዎቹ “ሉመን” እና “ፉድመርብል” የሚል መጠሪያ ያላቸው ሲሆን፥ መጠናቸው አነስተኛ በመሆኑ በኪሳችን ይዘን መንቀሳቀስ እንችላለን ተብሏል።

ተጠቃሚዎቹን ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም ሲፈልጉ በመሳሪያው ላይ ትንፋሻቸውን መተንፈስ ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው።

እያንዳንዱ መሳሪያ በመተግበሪያ አማካኝነት ከስማርት ስልኮቻችን ጋር የሚገናኙ ሲሆን፥ በዚህም የምግብ መፈጨት ስርዓታችን እና ሰውነታችን ምን ያክል ካሎሪ አቃጥሏል የሚለውን ያሳየናል።

“ሉመን” የሚል መጠሪያ ያለው የቴክኖሎጂ መሳሪያ በምንተነፍስበት ጊዜ በትንፋሻችን ወስጥ ያለውን የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መጠንም አንደሚለካ ነው የተነገረው።

በዚህም መሳሪያዎቹ ሰውነታችን ምን እያቃጠለ ነው ምን ያስፈልገዋል የሚልውን በመለየት ምን አይነት ምግብ መመገብ እንዳለብን እንደሚያሳውቁንም ነው የፈጠራው ባለቤቶች የተናገሩት።

እነዚህ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለገበያ በሚቀርቡበት ጊዜም በ299 የአሜሪካ  ዶላር እንደሚሸጥም የተቆረጠለት ዋጋ ያመለክታል።

ምንጭ፦ www.bbc.com

You might also like
Comments
Loading...