Fana: At a Speed of Life!

ቮልስዋገን በኢትዮጵያ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለመክፈት ስምምነት ገባ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ቮልስዋገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ኩባንያው በኢትዮጵያ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችለው ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የስልጠና ማዕከል መክፈትና ከቤት አውቶሞቢሎች ጋር በተያያዘ አዲስ መተግበሪያ የሚያስተዋውቅ ይሆናል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበባ አበባዬሁ እና ከሰሃራ በታች የቮልስዋገን ዋና ስራ አስፈጻሚ ቶማስ ሻፈር ተፈራርመውታል።

ከሰሃራ በታች የቮልስዋገን ዋና ስራ አስፈጻሚ ቶማስ ሻፈር ኢትዮጵያ በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የምትገኝ ሃገር መሆኗ ለኩባንያው እቅድ መሳካት ተመራጭ ያደርጋታል ብለዋል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜዬር እና የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተገኝተዋል።

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜዬር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

በእርሳቸው የተመራ የጀርመን የንግድ ማህበረሰብም አብሯቸው ኢትዮጵያ ገብቷል።

የዛሬው ስምምነትም በርካታ የጀርመን ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ ይረዳል ተብሏል።

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...