Fana: At a Speed of Life!

በ2018 በባህር ወደ አውሮፓ በሚደረግ ህገ ወጥ ስደት በአማካይ በቀን 6 ሰዎች ሞተዋል-ተመድ

አዲስ አበባ፣ጥር 23፣2011 (ኤፍቢሲ) ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በሜድትራኒያ ባህር ወደ አውሮፓ በሚደረግ ህገ ወጥ ስደት በአማካይ በቀን ስድስት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገለፀ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 2 ሺህ 275 የሚሆኑ ስደተኞች ባህር አቋርጠው አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ መሞታቸውንና የደረሱበት ያለመታወቁን ገልጿል።

በዚህ ህገ ወጥ የባህር ላይ ጉዞም በየቀኑ በአማካይ 6 ሰዎች ለህልፈት እንደተዳረጉም  ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባለፈም 13 ሺህ 300 የሚሆኑ ስደተኞች የሜድትራኒያንን ባህር አቋርጠው አውሮፓ መድርስ መቻላቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ይህ ቁጥርም ከባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ጋር ሲነፃፃር  ዝቅተኛ  መሆኑ ተገልጿል።

ስደተኞች ባህር አቋርጠው ሲሰደዱ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመከላከልም  የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

 

ምንጭ ፦news.un.org

 

You might also like
Comments
Loading...