Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ድል ሲቀናው ባህር ዳር ከነማ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ድል ሲቀናው ባህር ዳር ከነማ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ  ከተማዎች ሶስት ጨዋታዎች  ተከናውነዋል።

በዚህ መሰረትም የፕሪሜር ሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ቡና ስሑል ሽረን በአዲስ አበባ ሰቴዲየም አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት  በማሸነፍ መሪነቱን ማስጠበቅ ችሏል።

ለኢትዮጵያ ቡና በመጀመሪያው አጋማሽ ብቸኛዋን  ግብ አቡበክር ነስሮ  አስቆጥሯል።

ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ጨዋታውን ያካሄደው የጣናው ሞገድ ባህር ዳር ከነማ ደግሞ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመሸነፍ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በሌላ በኩል ደደቢትና ወላይታ ዲቻ ባደረጉት ጨዋታ ደደቢት 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በፕሪሜር ሊጉ የመጀመሪያውን ግብ እና ነጥብ ማግኘት ችሏል።

በተያያዘ ዜና ፋሲል ከነማ በነገው ዕለት ከወልዋሎ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ለማከናወን በዛሬው ዕለት መቐሌ ገብቷል።

አጼዎቹ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፣በመቐሌ 70 እንደርታ ደጋፊዎችና በክለብ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...