Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ በተነሳ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ በተነሳ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ፡፡

በሃገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ በምትገኘው ኪክዊት ከተማ በተነሳ ግጭት ሁለት የፖሊስ ባልደቦችና ሁለት ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተነግሯል፡፡

ግጭቱ በሃገሪቱ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ መነሳቱን ፖሊስ አስታውቋል።

በግጭቱ ከሞቱት በተጨማሪ 12 ዜጎች መቁሰላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በምርጫው ፌሊክስ ሺሴኬዲ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

ይሁን እንጅ የእርሳቸው ተፎካካሪ የሆኑትና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ አላቸው የሚባሉት ማርቲን ፋዩሉ ውጤቱን እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎም ግጭት ተቀስቅሷል ነው የተባለው።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሁለት አመት መዘግየት በኋላ በተጠናቀቀው 2018 የመጨረሻ ቀን መካሄዱ ይታወሳል።

የምርጫው ውጤት ፀድቆ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚደረግ ከሆነ፥ ሃገሪቱ ነጻነቷን ከተጎናጸፈችበት የፈረንጆቹ 19 60 ወዲህ የመጀመሪያው ይሆናል።

ምንጭ፡ – ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like
Comments
Loading...