Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ባለፈው ህዳር ወር ላይ ብቻ በተላላፊ በሽታዎች ምክንያት 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ25፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ባለፈው ህዳር ወር ላይ  ብቻ በአየርና መሰል መንገዶች አማካይነት በሚተላላፉ በሽታችዎች  ምክንያት 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል።

እንደ ሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር መረጃ  ባለፈው ህዳር ወር ላይ 636 ሺህ  722 የሚሆኑ ሰዎች በተላላፊ በሽታዎች ተጠቅተው ነበር ።

በበሽታው ተጠቅተው ከነበሩት ታማሚዎች ውስጥም 3 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸው ነው የተገለፀው።

በብዛት ሰዎችን ከሚያጠቁ ተላለፊ በሽታዎች ውስጥም ሄፖታይተስ፣የሳንባ ነቀርሳ፣ ቂጥኝ ፣ጨብጥ እና ኮሌራ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ።

የኮሌራ በሽታ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ተላላፊ በሽታ ሲሆን ፥በህዳር ወር ላይም ከፍተኛ  ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ህይዎት ሊቀጥፍ ችሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ገዳይነታቸው እየጨመረ የመጣውን እነዚህን ተላላፊ በሽታዎች ለመከላላከልም መንግስት የተለየዩ እቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ በተለይም በተበከለ አየር አማካይነት ከሰው ወደ ሰው ከሚተላለፉ በሽታዎች እራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው በዘገባው ተመላክቷል።

 

ምንጭ ፦ ቻይና ዴይሊ ዶትኮም

You might also like
Comments
Loading...