Fana: At a Speed of Life!

ማይክ ፖምፔዮ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ የነበራቸውን ፖሊስ ተቹ

አዲስ አበባ፣ጥር 02፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት አስተዳደር   በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ የነበራቸው ፖሊስ መተቸታቸው ተገለፀ።

ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ግብፅ መግባባታቸው ይታወቃል።

ማይክ ፖምፔዮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚያደርጉት ጉብኝት አላማ አሜሪካ ወታደሮችን ከሶሪያ ለማስወጣት መወሰኗን ተከትሎ ቅሬታ ከገባቸው አረብ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ነው ተብሏል።

ሚ ኒስትሩ በግብፅ በነበራቸውን ቆይታ በሰጡት መግለጫም የኦባማ አስተዳደር በመካከለኛው መስራቅ ላይ የነበራቸው የተሳሳተ ፖሊስ ቀጠናውን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎት መቆየቱን ተናግረዋል።

ስለሆነም አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ ያላትን ፖሊሲ በማስተካከል ከሀገራቱ ጋር መልካም የሆነ ግንኙነት የመመስረት ፅኑ ፍላጎት ያላት መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት  አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር በፀጥታ እና በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ መምከራቸው ተነግሯል።

ፖምፔዮ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ጋር ተገናኝተዋል።

ውይይታቸው ተከትሎም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅትም ፖምፔዮ ሀገራቸው ከመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት ጋር ጠንካራ ወዳጅነትዋን ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።

ፖምፔዮ በኢራቅ እና ጆርዳን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ የወታደሮች ከሶሪያ መውጣት አሜሪካ ከፅንፈኛው አይኤስ ጋር የምታደርገውን ውጊያ ታቆማለች ማለት አይደለም ሲሉ ለሀገራቱ መሪዎች ተናግረዋል።

 

ምንጭ፡- አልጀዚራ ና አህራም

You might also like
Comments
Loading...