Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማትያስ ህዝቡ አብሮነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በራሱ በመተሳሰብ አብሮነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ አስተላለፉ።
ፓትርያርኩ በጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ እርስ በራሱ በመረዳዳትና በመከባበር ሀገሩን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
ህዝቡ በመተሳሰብና በመረዳዳት አንድነቱን እንዲያጠናከርም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወጣቱ ራሱን ከኤች አይቪ ኤድስ መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።
የጸረ ቫይረሱን መድሀኒት የሚወስዱትም ፀበል ቢጠመቁም እንኳ መድሀኒታቸውን በሀኪም ምክር መሰረት በአግባቡ እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.