Fana: At a Speed of Life!

 ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  የሴቶች ማረፊያና ልማት ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተለያየ አይነት ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ህጻናት እንክብካቤ የሚያደርገውን የሴቶች ማረፊያ እና ልማት ማዕከል ጎበኙ፡፡

13 አመታትን ያስቆጠረው ማዕከሉ ስራውን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችም ቅርጫፎቹን ከፍቷል፡፡

ማእከሉ በዋናነት የተለያየ አይነት ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ስነ ልቦናዊ ድጋፍና የሙያ ስልጠናዎችን በመስጠት ህይወታቸው የተስተካከለ መንገድ እንዲይዝ ያደርጋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ማእከሉ የሚያከናውናቸውን ስራዎች የተመለከቱ ሲሆን፥ የማእከሉ ሰራተኞችን እና ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙትን ሴቶችንም አበረታተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዝደንት ሩፒ ባንዳ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሩፒ ባንዳ በኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች እየታየ ያለው የለውጥ ድባብ ለኢትዮጵያና ለአካባቢው ብቻ ሳሆን ሁሉንም አፍሪካዊ የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ጉዞ የአፍሪካውያን የስኬት ታሪክ ተደርገው ሊጠቀሱ ከሚችሉ ክስተቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚቀርብ ብለዋል በውይይታቸው ወቅት፡፡

ሀገሪቱ አሁን የተያያዘችው መንገድም ወደ ቀጣዩ የስኬት ምዕራፍ እንደሚያደርሳት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያና ዛምቢያ በብዙ ጉዳዮች ግንኙነት የመሰረቱ ሀገራት መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፥ በቀጣይነትም የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር መስራት እንደሚገባ መግለጻቸውን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

You might also like
Comments
Loading...