Fana: At a Speed of Life!

ግብፅና ፈረንሳይ በቀይ ባህር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብፅና ፈረንሳይ በቀይ ባህር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ መጀመራቸው ተገለፀ።

ሀገራቱ ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ በቀይ ባህር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ መጀመራቸውን የግብፅ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጋራ ወታደራዊ ልምምዱም ከሁለቱ ሀገራት ወታደሮች በተጨማሪ በርካታ የጦር መርከቦች የተሳተፉበት መሆኑ ነው የተገለፀው።

የወታደራዊ ልምምዱ ዋና አላማም የሀገራቱን የባህር ሀይል የመከላከል አቅም ማሳደግና ቀጠናውን ከምንም አይነት ስጋት ነፃ ማድረግ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ልምምዱ በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ የባህር ላይ ወንበዴዎችና አሸባሪዎች የሚፈፅሙትን ትንኮሳ በጋራ ለመከላከል የሚረዳ መሆኑ ነው የተገፀው።

ሀገራቱ ባለፈው ህዳር ወር መጀመሪያ ላይም በቀይ ባህርና ሜዲትራንያን ባህር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸው በዘገባው ተመላክቷል።

ቀይ ባህር የባህረ ሰላጤው ሀገራት የተፈጥሮ ነዳጅ ዘይት ምርታቸውን በግበፅ ስዊስ ካናል በኩል ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሚያስተላልፉበት ዋነኛ የንግድ መስመር ነው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ ካይሮ እና ፓሪስ በቀጠናው በሚከሰቱ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እና በትብብር ለመስራት ስምምነት መፈፀማቸው ይታወሳል።

ምንጭ ፦አናዶሉ

 

You might also like
Comments
Loading...