Fana: At a Speed of Life!

የ13ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል መርሃ ግብር አካል የሆነ የጎዳና ላይ የሙዚቃ ትርኢት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ13ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል መርሃ ግብር አካል የሆነ የጎዳና ላይ የሙዚቃ ትሪኢት ተካሄደ።

የ13ኛው የብሄር ብረሰቦችና ህዝቦች በዓል ታዳሚዎች በሳምነቱ ወደ መዲናዋ የገቡ ሲሆን፥ የበዓሉ አካል የሆኑ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲካሄዱ ቆይተዋል።

ከነዚህም መካከል የፓናል ውይይት፣ ሲንፖዚየምና ጥናታዊ ጽሁፎች ሲቀርቡ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ተወካዮች በብሄር ብሄርሰቦችና ህዝቦች አልባሳትና መዋቢያዎች አጊጠው በብሄራዊ ትያትር አካባቢ በቡድን በቡድን ሆነው በመንገድ ላይ ባህዊ የሚዚቃ ትርኢትና ውዝዋዜዎችን ሲያቀርቡ አምሽተዋል።

በትርኢቱ ላይ የነበሩ ተሳታፊዎች መሰል ፕሮገራሞች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እርስ በእርስ ልምድ ለመለዋወጥና ለመተዋወቅ የሚስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሮግራሙ የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን ብዝሃነትና አንድነትለማጠናከር እንደሚያስችልም ነው የተናገሩት።

ከደቂቃዎች በኋላም በብሄራዊ ትያትር የሙዚቃ ድግስ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተገለጸው።

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ደረጃ 13ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ይከበራል።

በአፈ ወርቅ አለሙ

You might also like
Comments
Loading...