Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የሚውል የ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ብድር ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ህዳር 28፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራና ለዜጎች የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት የሚውል የ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት መፈፀማቸው  ተገለፀ።

ስምምነቱንም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ ተፈራርመውታል።

የብድር ስምምነቱ ኢትዮጵያ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እያከናወነች ላለችው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ወሳኝ መሆኑን  አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።

ብድሩ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የሚለሙ አካባቢዎችን ከማሳደግ በጠጨማሪ በአየርን ንብረት ለውጥ የሚመጣውን ችግር በመቀነስ የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

ኢትዮጵያም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃውን ለማጠናከርና የዜጎችን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት ፕሮግራምና እቅዶችን አውጥታ እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፥ የዓለም ባንክ ያደረገው ድጋፍም ይህንን ለማጠናከር ይረዳል ብለዋል።

ብድሩም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል የሚገኙ 645 ሺህ አባ ወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የአለም ባንክ ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ላይ የምታከናውነውን ተግባር አድንቀው ባንኩ ይህን ለማጠናከር የሚያስችል ብድር ሰጥቷል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ብክለትን ለመከላከል፣ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ለማከናወን በምታደርገው ጥረት የዓለም ባንክ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።

 

 

 

 

 

 

  

 

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...