Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረትና ፈረንሳይ ለሳህል ቀጠና 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረትና ፈረንሳይ በሳህል ቀጠና ውስጥ ለሚገኙ አምስት ሀገራት የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉ ታጣቂዎችን ለመከላከል አላማውን ላደረገ የልማት ፕሮግራም የሚውል መሆኑም ተገልጿል።

ይህ የተሰማው በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈው የአምስቱ ሀገራት ጥምረት በሞሪታንያ በተሰበሰበበት ወቅት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

አምስቱ ሀገራት በአካባቢው የተንሰራፋውን ሽብርተኝነት ለመከላከል የጋራ ጥምረት ከዚህ ቀደም መመስረታቸው ይታወሳል፡፡

ከተለገሰው ድጋፍ ውስጥ 900 ሚሊየን ዶላሩን የአውሮፓ ህብረት የሰጠ ሲሆን ቀሪው ከፈረንሳይ መንግስት የተገኘ ነው፡፡

ሞሪታንያ በተደረገው ስብሰባ ላይ እንደተነሳው የአውሮፓ ሃገራት የስደተኞችን ፍሰት መግታት የሚፈልጉ ከሆነ፥ በቀጠናው በመሰረተ ልማትና በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንዳለባቸው ገልጻለች።

በቀጠናው ሽብርተኝነት ለመዋጋት ጥምረት የፈጠሩት ሀገራት ኒጀር፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ማሊ እና ሞሪታንያ ናቸው፡፡

 

ምንጭ፦አልጀዚራ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...