Fana: At a Speed of Life!

የአነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ከተቀመጠው ግብ አንፃር አፈፃጸሙ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማት በ2012 በአጠቃላይ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ የ8 በመቶ ለማድረስ ካስቀመጠው ግብ አንፃር አፈፃጸሙ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዘርፉ በሚታዩ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአዳማ ከተማ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለፀው ዘርፉ በ2007 ዓ.ም የ5 በመቶ በኢኮኖሚው ውስጥ ድርሻ የነበረው ሲሆን፥ በ2011 ዓመተ ምህረት የ6 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ ላይ ደርሷል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ እንዳሉት፥ የኢንዱስትሪ ልማት አስተማማኝና ሰፊ መሰረተ ልማት ያለው ተወዳዳሪ የአነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪ እንዲኖረው መንግስት ያላለሰለሰ ጥረት እያደረገ ነው።

የጥሬ እቃ አቅርቦት፣ የክህሎት፣ የፋይናንስ መሰረተ ልማቶችና ሌሎችም ችግሮች በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድግ ማነቆ ሆነዋል ነው ያሉት።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በ2012 ዓ.ም በዘርፉ ከ27 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው።

በአፈወርቅ አለሙ

You might also like
Comments
Loading...