Fana: At a Speed of Life!

የቱርኳ ኢስታንቡል በባቡር ለመጓዝ ገንዘብ ሳይሆን የውሃ መያዣ ፕላስቲኮችን መጠየቅ ጀምራለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀደም ብሎ ቁስጥንጥንያ በመባል ትጠራ የነበረችው የቱርኳ ግዙፍ ከተማ ኢስታንቡል በባቡር ጣቢያዎቿ ላይ ያልተለመደና አዲስ የክፍያ ስርዓት መጀመሯ ተሰምቷል፡፡

ይህ አዲስ የሙከራ የክፍያ ስርዓት ተግባራዊ መሆን የጀመረው በባቡር ጣቢያዎች ውስጥ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በርግጥ የክፍያ ስርዓቱ ከዚህ ቀደም እንደተለመደው የወረቀት ገንዘብ አሊያም የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አይደለም ተብሏል፡፡

ሆኖም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመጓዝ የውሃ መያዣ ፕላስቲኮችን በመክፈል የሻዎት ቦታ መድረስ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

የውሃ መያዣ ፕላስቲኮቹን ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁ ማሽኖች ውስጥ በሚጨምሩበት ወቅት የመጓጓዣ ትኬት እንደሚያገኙም ተገልጿል፡፡

ኢስታንቡል ሁለቱን አህጉሮች ማለትም አውሮፓንና እሲያን በማስተሳሰር የምትታወቀው ግዙፍ ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡

ታዲያ አዲሱ የክፍያ ስርዓት ይህችን ግዙፍ ከተማ የሚገጥማትን አካባቢያዊ ብክለት ይክላከላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

እስከአሁን የክፍያ ስርዓቱን የሚያቀላጥፉ ማሽኖች በሦስት ጣቢያዎች ውስጥ የተገጠሙ ሲሆን፥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ እንደሚተከሉም የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

ቱርክ በየዓመቱ 31 ሚሊየን ቶን አላቂ ዕቃዎች የሚከማቹባት ሲሆን፥ 11 በመቶ ያህሉን መልሳ ጥቅም ላይ እንደምታውል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ይህንን ቁጥር ለመቀየርም በአምስት ዓመታት ውስጥ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውሉ አላቂ ነገሮችን ወደ 35 በመቶ ለማሳደግ ማለሟን የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

 

ምንጭ፦አልጀዚራ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...