Fana: At a Speed of Life!

አብዴፓ 72 አባላቱን በክብር አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) 72 አባላቱን በክብር አሰናበተ።

የአብዴፓ ሊቀመንበርና የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ሀጂ ስዩም አወል እና ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ 72 የድርጅቱ አባላት የተሰናበቱት በሰመራ አየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው መደበኛ ጉባኤ ነው።

የተሰናበቱት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራርና አባላቱ በክልሉ በነበራቸው የስራ ዘመን ላበረከቱት ሚና የምስጋና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።

ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬ ውሎው የባለፉትን 3 አመታት የኦዲት ሪፖርት ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን በነገው ዕለት ተተኪ አመራሮች ምርጫ ያካሄዳል።

በሶዶ ለማ

You might also like
Comments
Loading...