Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን በ12 ቀናት 150 ሴቶች ተደፍረዋል-ተመድ

አዲስ አበባ፣ህዳር፣ 25፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ሱዳን ባለፉት 12 ቀናት ውስጥ 150 ሴቶች እንደተደፈሩና የተለያዩ ፆታዊ ጥቃቶች እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

ቤንቲኡ በተባለች ከተማ ሰሜናዊ ክፍል መለዮ የለበሱ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት መፈፀማቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚገኙ ኤጀንሲዎች ይፋ አድርገዋል።

ጥቃቱን በማውገዝ ባወጡት መግለጫ አስፀያፊ እርምጃ ነው ያሉ ሲሆን፥ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጥፋተኞች ለህግ ማቅረብና ፍትህ መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ድንበር የለሹ የህክምና ቡድን ባለፈው ሳምንት 125 ሴቶች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ወደ ሚቀርብበት ማዕከል በሚጓዙበት ወቅት መደፈራቸው አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒኦ ጉቴሬዝ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን፥ በደቡብ ሱዳን መሪዎች መከካል ስምምነት የተደረሰ ቢሆንም ለሴቶችና ህፃናት አስጊ የሆኑ ነገሮች እንደቀጠሉ ናቸው ብለዋል።

ሁሉም ባለድርሻ አካላት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል በአስተያየታቸው።

በደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ግጭት ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ፆታዊ ጥቃቶች አሳሳቢና አስደንጋጭ መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

 

ምንጭ፥ አልጅዚራ

You might also like
Comments
Loading...