Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ደረጃ በአልባሳት ዘርፍ ታዋቂ ምልክት ካላቸው ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሆንግ ኮንግ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 2 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልዑክ በዓለም ደረጃ በአልባሳት ዘርፍ  ታዋቂ ምልክት ካላቸው ተቋማት  ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሆንግ-ኮንግ ውይይት አደረገ።

በውይይቱ ኩባንያዎቹ የኢትዮጵያን ምርት እንዲገዙና ለእነሱ ምርታቸውን በማቅረብ ላይ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ፋብሪካዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንዲያበረታቷቸው ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

የፒ ቪ ኤች ምክትል ፕሬዚዳንት በሆንግ-ኮንግ ተገኝተው በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያላቸውን መልካም ተሞክሮ ለብራንድ አመራሮቹ ገልጸዋል።

ተሳታፊዎቹም ዘርፉን ለማሳደግ በትብብር እየተሰራ ያለውን ሂደት ያደነቁ ሲሆን፥ በተለይ ዘላቂ እንዲሆን በዕውቀት ላይ ተመስርቶ የተሄደበት ርቀት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት የመጨረሻ ማረፊያ የሆነችውን አፍሪካን እንዲሁም ኢትዮጵያን ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በተጨማሪም እነዚህ አለም አቀፍ ተቋማት ከኢትዮጵያ ጋር  በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ አቋም ያላቸው መሆኑ ነው የተገለፀው።

 

You might also like
Comments
Loading...