Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 75 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኦሮሚያ ክልል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 75 መድረሱን የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ ከበደ፥ ኮሚሽኑ በዘጠኝ ቅርንጫፎቹ ሲያካሂድ በነበረው ምርመራ ዙሪያ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም እስካሁን በተከናወነው የማጣራት ስራ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

እስካሁን በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም፦

ከኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ተቋም

አቶ ተሾመ ለገሰ- ዋና ዳይሬክተር

አቶ ተሾመ ከበደ- የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል

ወይዘሮ መስከረም ዳባ- የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል

ከኦሮሚያ ግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ አመራር የነበሩ እና በአሁኑ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ

አቶ መሃመድ ቃሲም- ዋና ዳይሬክተር

አቶ እንዳልካቸው በላቸው- የኤጀንሲው የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል

አቶ ይልማ ዴሬሳ- የኤጀንሲው የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል

አቶ አብዶ ገለቶ፦ የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር

አቶ መንግስቱ ረጋሳ፦ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚሮ ምክትል ሀላፊ የነበሩ በአሁኑ ወቅት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ

ከሻሸመኔ ከተማ

አቶ ፈይሳ ረጋሳ፦ የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ

አቶ አብዶ ገበየሁ፦ የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ

አቶ ገመዳ በዳሶ፦ የሻሸመኔ ከተማ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ

ከጅማ ዞን

አቶ ፋንታ በቀለ፦ በጅማ ዞን የማንቾ ወረዳ አስተዳዳሪ

በአጠቃላይ እስካሁን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉየመንግስት የስራ ሀላፊዎች ቁጥር 75 መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በሙለታ መንገሻ

You might also like
Comments
Loading...