በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደዋል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዛሬው ዕለት በክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
በርካታ ተመልካቾችን ያስተናገገደው የፋሲል ከነማና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ሌላኛው ጨዋታ 1 ለ 1 ነው የተጠናቀቀው።
በጨዋታው ለባለሜዳዎቹ ዳዋ ሁቴሳ በ37ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር የሲዳማ ቡናን የአቻነት ግብ አዲስ ግደይ ማስቆጠር ችሏል።
ወላይታ ድቻ መቐለ 70 እንደርታን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት እንግዳውን ቡድን ማሸነፍ ችሏል።
ወላይታ ወሳኝ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ ያስቻለችውን ግብ ፀጋዬ አበራ በ82ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በሌላ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተላያይተዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ስሑል ሽረን አስተናግዶ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸናፊ ሆኗል።
ግቦችንም አሜ አህመድ በ25ኛው ምንተስኖት አዳነ በ65ኛው እና አቤል ያለው በ83ኛውና 93ኛው ደቂቃ ላይ የፈረሰኖችን ግብ አስቆጥረዋል።