Fana: At a Speed of Life!

በቂ የእግር ጉዜ አላደረጋችሁም በሚል ሰራተኞቹን በገንዘብ የሚቀጣው የቻይና ኩባንያ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና የሪል እስቴት ኩባንያ ሰራተኞቹ የአካል ብቃት እንቀስቃሴ እንዲያደርጉ ለማስገደድ የሚከተለው መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል።

ኩባንያው በወር ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ያክል የእግር ጉዞ የማያደርጉ ሰራተኞቹን በእያንዳንዱ እርምጃ በገንዘብ እየቀጣ መሆኑም ተነግሯል።

እንደ ኩባንያው ሰራተኞች ገለፃ እያንዳንዱ ሰራተኛ በወር ውስጥ መጓዝ ያለበት 180 ሺህ እርምጃ ነው፤ ይህን ካላሟሉ ግን በእያንዳንዱ እርምጃ የ0 ነጥብ 01 የቻይና ዩዋን ቅጣት እንደሚያስከፍላቸው ተናግረዋል።

አሁን አሁን በቻይና ውስጥ የእግር ጉዞ ማድረግ ትልቅ ነገር እየሆነ መጥቷል የተባለ ሲሆን፥ በርካታ ኩባንያዎቸም ሰራተኞቻቸው ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን እንዲሰሩ እያበረታቱ ይገኛሉ።

ለአብነትም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ደንበኞቻቸው በቀን ውስጥ ምንያልክ እርምጃ ወይም የእግር ጉዞ እንደሚያደርጉ በመተግበሪያ የሚከታተሉ ሲሆን፥ የሚጠበቅባቸውን ያክል ለተጓዙትም የዋጋ ቅናሽ ያደርጋል ተብሏል።

ትምህርት ቤቶቸም ተመሪዎቻቸው የአካል ብቃት አንቀስቃሴን አዘውትረው አንዲሰሩ እያስገደዱ ነው የተባለ ሲሆን፥ የሪል እስቴት ኩባንያው የመጣበት መንገድ ግን አነጋጋሪ ሆኗል።

አንድ የቻይና ጋዜጣ እንዳስነበበው በጓንዡ ከተማ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ስሙ ያልተጠቀሰው የሪል እስቴት ኩባንያ ነው ሰራተኞቹ በወር ውስጥ ቢያንስ 180 ሺህ እርምጃ የእግር ጉዞ እንዲያደርጉ መስፈርት ያስቀመጠው።

በወር የሚጠበቅባቸውን ያክል የእግር ጉዞ ላደረጉ ሰራተኞቹ ምንም አይነት ሽልማት የማይሰጠው ኩባንያው፤  ይህንን የማያሟሉትን ደግሞ በገንዘብ እየቀጣ መሆኑ ነው የተነገረው።

አንድ የኩባንያው ሰራተኛ እንዳስታወቀው በወር ውስጥ መጓዝ ከነበረበት የ180 ሺህ እርምጃ ውስጥ 10 ሺህ ያክሉን ሳያሟላ በመቅረቱ እያንዳንዱ እርምጃ በ0 ነጥብ 01 ዩዋን ተባዝቶ በድምሩ 100 የቻይና ዩዋን ከፍሏል።

እያንዳንዱ ሰራተኛም በወር ውስጥ የሚጠበቅበትን የ180 ሺህ እርምጃ የእግር ጉዞ ለማሟላትም በየእለቱ በአማካኝ 6 ሺህ እርምጃዎችን መጓዝ እንዳለበትም ነው ሰራተኞቹ የሚናገሩት።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com

You might also like
Comments
Loading...