Fana: At a Speed of Life!

ሳምሰንግ በቻይና የሚገኘውን የሞባይል ስልክ ማምረቻ ማዕከሉን ሊዘጋ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ4፣2011(ኤፍ.ቢ.ሲ)ሳምሰንግ የኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ በቻይና ሰሜናዊ ግዛት  ቲያንጂህ ከተማ የሚገኘውን የተንቀሳቃሽ ስልክ ማምረቻ ማዕከሉን ሊዘጋ ነው ።

ኩባንያው ማዕከሉን ለመዝጋት የወሰነበት ምክንያትም በሀገሪቱ ስልኮችን በቀላል ወጪ በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ከሚያደርሱ ድርጅቶ ጋር ያለውን  ከፍተኛ የገበያ ውድድር መቋቋም ባለመቻሉ ነው ተብሏል

በዚህ ምክንያትም ኩባንያው በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በቻይና የነበረው የሽያጭ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል።

በመሆኑም ኩባንያው በሚቀጥለው የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጀምሮ ማዕከሉን የሚዘጋ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ሳምሰንግ  2 ሺህ 600 የሚሆኑ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረውን ማዕከል መዝጋት ማሰቡም ብዙ ሰራተኞችን ማስደንገጡ ተነግሯል ።

ይሁን እንጂ ኩባንያው ድርጅቱን በሚዘጋበት ወቅት ሰራተኞችን  ወደ ሌላ ማዕከሉ ከማዘዋወር በተጨማሪ የተለያዩ ማካካሻዎችን የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

ኩባንያው ቻይና በሚገኘው በዚህ ማዕከል በዓመት ውስጥ 36 ሚሊየን የስልክ ቀፎዎችን  በማምረት ለገበያ ያቀርብ እንደነበርም በዘገባው ተመላክቷል።

በዓለም ደረጃ ተቀባይነትን ያተረፈው ግዙፉ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ሳምሰንግ የተለያዩ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ  ስልኮችንና  የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በማምረትና በማከፋፈል ይታወቃል።

 

ምንጭ ፦ሲጂቲኤን

 

You might also like
Comments
Loading...