Fana: At a Speed of Life!

ማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆን ማሰናበቱ ተነግሯል።

በዚህም መሰረት አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ከሁለት ዓመት ተኩል የማንችስተር ዩናይትድ ቤት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ክለብ ባወጣው መግለጫ፥ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት በቆዩበት ወቅት ለሰሩት ስራ በማስመስገን፤ በቀጣይም ስኬትን ተመኝቶላቸዋል።

ጆሴ ሞሪኒሆን የሚተካ አሰልጣኝ እስኪቀጠር ድረስ ክለቡን በአደራ ተቀብሎ የሚያሰለጥን ሰውም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ነው ክለቡ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...