Fana: At a Speed of Life!

ማርዮት የ500 ሚለየን ደንበኞቹ መረጃ መበርበሩ ተከትሎ ለቅያሪ ፓስፖርት ክፍያ መፈጸም አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማርዮት ዓለምአቀፍ ሆቴል 500 ሚሊየን ደንበኞች መረጃ በርባሪዎች እጅ መግባቱ ባለፈው ሳምንት ተገልጿል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የተሰረቁት የፓስፖርት መለያዎችን ለመተካት ማርዮት ለደምበኞቹ ክፍያ መፈጸም አለበት እየተባለ ይገኛል፡፡

በተጠቃሚው ጥያቄ አዲስ የፓስፖርት መለያ ለማውጣትም በአሜሪካ 110 ዶላር እንደሚያስከፍል ተገልጿል፡፡

ማርዮት በምርመራው በርባሪዎቹ የደንበኞችን መረጃ ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ መውሰድ እንደጀመሩ አስታውቋል፡፡

ከተሰረቁት መረጃዎች መካከልም የደንበኞች ስም፣ የባንክ አካውንት ቁጥር፣ ፓስፖርት ቁጥር፣ የፆታ መለያና የመሳሰሉት መረጃዎች በመንታፊዎች እጅ መውደቃቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

ማርዮት ግዙፍ ስም ያላቸው ሆቴሎችን የሚያስተዳድር ሲሆን፥ በስሩም ሸራተን፣ ደብሊው (w) ሆቴልስ፣ ለ መሪዲያን የተባሉ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ሁሉም የማርዮት ሆቴሎች ደንበኞቻቸውን ለማስተናገድ የተናጠል ኔትወርክ ይጠቀሙ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

የማርዮት ደንበኞች መረጃ በዚህ ያህል ቁጥር በበርባሪዎች እጅ ሲወድቅ ከያሁ ኩባንያ ቀጥሎ ትልቁ ነው ተብሎለታል፡፡

 

 

ምንጭ፦ፎክስ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...